በስጋትና በተስፋ የተሞላው መጪው ጊዜ

ዋንዳ ካጋጠማትና ማቅ ካስለበሳት ታሪኳ ውስጥ የሁቱና ቱትሲ ጎሳዎች የእርስ በርስ ጭፍጨፋ በዋነኝነት ይነሳል። በጽንፈኛ ሁቱዎች አነሳሽነት፣ በአውሮፓውያን ሀገራት የመሳሪያ ድጋፍ ወደ 800 ሺ ቱትሲዎች ህይወታቸውን ሊነጠቁ ችለዋል። ከዚህ ጥቁር ታሪክ ውድመት ትምህርት የቀሰመችው ሩዋንዳ፣ በዘር መከፋፈልን በህግ የሚያስጠይቅ እንዲሆን በማድረግ ከሀገሯ በማስገድ አርአያ መሆን ችላለች።

በአንጻሩ በኢትዮጵያ የሚንጸባረቀው ብሔር ተኮር ፌዴራልዝም መዘዝ በርካቶችን ለሞት ተዳርገዋል። በሺ የሚቆጠሩትን ለአካል ጉዳት እንዲሁም ሚሊዮኖችን ከቀያቸው እንዲፈናቀሉ ሰበብ ሆኗል። ከሩዋንዳ ትምህርት መውሰድ ያቃተው የኢትዮጵያ ፖለቲካ፣ አሁንም ማንነትን መሰረት ባደረጉ እንቅስቀቀሴዎች ሀገሪቱ እየታመሰች ትገኛለች።

ምንም እንኳን ዜግነትን መሰረት ያደረጉ የፖለቲካ እንቅስቀሴዎች መቀንቀን ቢጀምሩም፣ ያላቸውን አጀንዳ ለህዝብ እንዳያደርሱ በብሔር ፖለቲካ የተቃኘው አመለካከት አሁንም እያሳደዳቸው ለመሆኑ በየጊዜው የሚደርስባቸው ግድያ፣ እንግልት፣ እስርና ማስፈራራት ማሳያ መሆን ይችላል። ችግሩን የበለጠ አስከፊ የሚያደርገው ደግሞ ንጹሃን ዜጎች የዚህ ዒላማ መሆናቸው ነው።

Continue reading

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*