ቤቶችን የመሸጥና የማፍረስ እሰጥ-አገባ

አብዛኛው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ የቤት ችግር የሚያንገላታው እንደሆነ ሲነገር ይደመጣል። ቁጥራቸው ጥቂት የሆኑት አቅማቸው በፈቀደ መጠን ቆጥበውና በዚያ ላይ እድለኛ ከሆኑ የጋራ መኖሪያ ቤት ይደርሳቸዋል። ቁጥሩ የሚያይለው ግን አሁንም ገንዘብ እየቆጠበና እድሉን እየተጠባበቀ በኪራይ እየተሰቃየ ነው። መንግስት የቤት ችግሩን ለመቅረፍ የተለያዩ ውጥኖችን እንዳወጣ ቢናገርም፣ በአንጻሩ እየተደረጉ ባሉት ህገወጥ ድርጊቶች የቤት ተስፋው በመንጠፍ ላይ ይገኛል።

ሌላኛው የህብረተሰብ ክፍል ደግሞ መንግስት በሰጠው ቤት በተለምዶ የቀበሌ ቤት ውስጥ በዝቅተኛ ዋጋ እየከፈለ ይኖራል። አዲስ አበባ ውስጥ ከመቶ ሺዎች በላይ የሚቆጠሩ የቀበሌ ቤቶች እንዳሉ ይነገራል። ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በእነዚህ የቀበሌ ቤቶች ጉዳይ ላይ የተለያዩ አቋሞች ሲያንጸባርቀ መመልከት ተችሏል።

ለአብነትም የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትሕ-ኢዜማ ስለከተማዋ የቤቶች እጥረት መፍትሔ ያለውን እቅድ ሲያቀርብ፣ ‹‹የቀበሌ ቤቶችን የከተማዋ አስተዳደር በሚያወጣው የጥራት ደረጃዎች መሰረት፣ በቤቶቹ ለሚኖሩት ቅድሚያ በመስጠት የቤቶቹን ባለቤትነት በሁለት ዓመታት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ከመንግስት ወደ ነዋሪዎች በሽያጭ ማዘዋወር›› እንደሚል በመተዳደሪያ ደንቡ ሰፍሯል።

Continue reading

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*