
ከአፄ ኃይለስላሴ ዘመነ መንግስት ጀምሮ የአደባባይ በዓላት ሲከወኑበት የነበረው መስቀል አደባባይ፣ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚከበረውን የመስቀል በዓል ይከበርበት ስለነበር ስያሜው ከዚያ እንደመጣ መረጃዎች ያስረዳሉ። ንጉሱን ከስልጣን ያስወገደው ደርግ በበኩሉ፣ ስያሜውን ወደ አብዮት አደባባይ በመቀየር አብዮት በዓላት ጨምሮ የመስቀል በዓል እንዲከበርበት አድርጓል። በዘመነ ኢህአዴግ ደግሞ ስያሜው ወደቀድሞ መስቀል አደባበይ ተመልሶ፣ ከፖለቲካ እስከ ኪነ ጥበብ እንዲሁም ኢሬቻንና የታዋቂ ሰዎች የአስከሬን ሽኝት እና ሌሎች መሰናዶዎችን ሲያስተናግድ እዚህ ደርሷል።
ይሄ ዘርፈ ብዙ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘው አደባባይ፣ የዶ/ር ዐቢይ አስተዳደር ወደ ስልጣን ከመጣ ወዲህ የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጥ በማሰብ የማስፋፊያና ተጨማሪ ግብአቶች በመጨመር ግንባታ ተደርጎለታል። ከግንባታው በኋላም የተለያዩ መርሃ ግብሮችን በማከናወን ላይ ይገኛል።
ለአንድ ወር ያክል በጾም ላይ የቆዩት የእስልምና እምነት ተከታዮች፣ ፆሙ ከመገባደዱ በፊትና የኢድ አልፈጥር በዓል ከመከበሩ አስቀድሞ በአደባባይ ላይ ለሚደረግ የኢፍጥር ሥነ ሥርዓት የከተማ አስተዳደሩን በጠየቅ ዝግጅት ሲከናውኑ ነበር። ይሁን እንጂ ‹‹ከታቀደው ዓላማ ውጪ ናቸው›› የተባሉ (ግለሰቦች) አካላት መስቀል አደባባይን ወደ ‹‹ኢድ አደባባይ›› እንለውጣለን በማለታቸው ተቃውሞ አስነስቶ ነበር።
Be the first to comment