አሸባሪ የተባለው “ሸኔ” አነጋጋሪነቱ ቀጥሏል

የሚንስትሮች ምክር ቤት ባካሄደው ስብሰባ ህወሓትን እና ሸኔን በአሸባሪ ድርጅት እንዲፈረጁ መስማማቱን በማስታወቅ፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውሳኔ እንዲሰጥበት ጥያቄ አቅርቧል። የዜናውን መውጣትን ተከትሎ የተለያዩ አስተያየቶች ሲደመጡም ነበር። አንዳንዶች “ሸኔ” የሚባል ድርጅት በሌለበት አሸባሪ መባሉን ሲያሰተባብሉ፣ ሌሎች ደግሞ ከመዘግየቱ በስተቀር ተገቢ ውሳኔ ነው ይላሉ።

የኢትዮጵያ ህገ መንግስት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ 55(1) ፣ ‹‹ሽብርተኛ ድርጅት›› ማለት ሰዎችን በማገት ወይም በመጥለፍና እንደመያዣ በማድረግ ከመንግስት ጋር የሚደራደር እንዲሁም የሚፈልገው ነገር ተፈጻሚ ካልሆነለት የያዛቸውን ሰዎች ‹‹እንደሚገድል ወይም እንደማይለቅ የሚዝት›› ድርጅት ነው ይላል። በተጨማሪም የሀገር ሀብትንና ንብረት ላይ አደጋ ያደረሰ፣ ሰዎችን የገደለ አሊያም ለአካል ጉዳት የዳረገ፣ የህብረተሰቡን ደህንነትና ጤና ለአደጋ ያጋለጠ እንዲሁም የህዝብ አገልግሎቶችን ለከፍተኛ አደጋ ያጋለጠ፣ የተቆጣጠረ አሊያም እንዲበላሽና እንዲቋረጥ በማድረግ የተሳተፈ ነው ይላል። በዚህ ድርጊት የተሳተፈም ከ15 ዓመት እስከ እድሜ ልክ በሚደርስ ጽኑ አስራት ወይም በሞት የሚያስቀጣ ወንጀል ነው ሲል ይደነግጋል።

ብዙዎች እንደሚስማሙበትም “ኦነግ ሸኔ”(“ሸኔ”) እና ህወሓት ከላይ የተገለጹትን የሽብር ድርጊቶች ስለመፈጻማቸው በርካታ መረጃዎችን መጥቀስ እንደሚቻል ያነሳሉ። ድርጅቶቹ የጦር መሳሪያ ከመታጠቃቸውና ከሚያደርጓቸው ኢ-ሰብአዊ ድርጊቶች በመነሳት እና በህዝብ ተቋማት ላይ የሚያደርሱት ውድመትን በመዘርዘር ውሳኔው የዘገየ ከመሆኑ ውጪ ተገቢ እንደሆነ ያስረዳሉ።

Continue reading

 

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*