አንጻራዊ ሠላምና የዜጎች ግድያ

ኦሮሚያ ክልል ማንነትን መሰረት ያደረገው የዜጎች ግድያ ለሁለት ሳምንታት መሻሻል ቢታይበትም፣ አሁንም ግን ሙሉ ለሙሉ እንዳልተቀረፈ ይስተዋላል። ለዚህም እንደ ምክንያት እየተነሳ የሚገኘው፣ በክልሉ ያለውን የጸጥታ ችግር ለመቅረፍ መንግስት ከዚህ ቀደም በተለየ መልኩ እየወሰደ የሚገኘው እርምጃ ይጠቀሳል። በሌላ በኩል በትጥቅ የታገዘ እንቅስቃሴ እያደረገ የሚገኘው ‹‹ሸኔ›› በሽብርተኝነት መፈረጁም ለአካባቢው መረጋጋት እንደ ተጨማሪ ምክንያት ነው እየተባለ ይገኛል።

ይሁን እንጂ በያዝነው ሳምንት በክልሉ የተከሰቱት ሁለት ግድያዎችን ብንመለከት እንኳን፣ በታጣቂው ‹‹ሸኔ›› መገደሉን የተሰማው የኦቢኤን ጋዜጠኛ ጉዳይ እንዲሁም፣ ‹‹የታጣቂው ቡድን አባል ነው›› የተባለ ወጣት በመንግስት ጸጥታ አካለት የደረሰበት ማሰቃየት፤ አንዳንዶች እንደሚሉት ደግሞ ግድያ ማሳያ ናቸው።

ብዙም ያልተነገረው የጋዜጠኛው ሲሳይ ፊዳ ግድያ ሁኔታ ከዚህ ቀደም በኢዜማ እጩ ተወዳዳሪ ላይ የተደረገው አይነት ግድያ ጋር መመሳሰሉ የግጥምጥሞሽ እንደማይመስል የሚናገሩ አሉ። ሁለቱም ከሰርግ ፕሮግራም በመመለስ ላይ እያሉ መገደላቸው፣ በግድያው ማስተላፍ የተፈለገ አጀንዳ አለ የሚል አስተያየት እንዲሰነዘር አስችሏል። ከዚህ አንጻር ዜጎች በተለይም በኦሮሚያ ክልል የሚኖሩ በሰላም ወጥተው መግባት አሁንም ዋነኛው ጉዳይና አሳሳቢ መሆኑ አመላካች ነው።

Continue reading

 

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*