
በትግራይ ክልል የተደረገውን ህግ የማስከበር ሂደት ተከትሎ ወደ ጫካ የሸሸው የህወሓት ቡድን በሱዳን በኩል ለማምለጥ ሙከራ እያደረገ እንደሆነ በተደጋጋሚ ይሰማል። ይህንን ተከትሎ የመከላከያ ሰራዊት የአሸባሪው ቡድን ያመልጥባቸዋል ተብሎ በሚገመቱ አካባቢዎች ጥብቅ ቁጥጥር እያደረገ እንደሆነ ተነግሯል። ከሳምንታት በፊት የመከላከያ ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫ፣ የህውሓት ከፍተኛ አመራሮች በወታደሮቻቸው እና አጃቢዎቻቸው ከለላ ተሰጥቷቸው ወደ ሱድን ሊሸሹ ሲል በተወሰደ እርምጃ ወደ ዋሻቸው እንደተመለሱ እና ከሀገር ለመውጣት ያላቸው ተስፋ ማብቃቱ ተገልፆ ነበር። የማንሰራራት ተስፋው የተሟጠጠ የሚመስለው ቡድኑ፣ በተለይም መጪው ጊዜ የክረምት ወር ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በተለያዩ ግንባሮች ጦርነት በመክፈት የተከዜ ወንዝ ሳይሞላ ከአገር ለመውጣት እልህ አስጨራሽ ሙከራዎችን እየሞከረ ነው። ይህንንም ሙከራ ለማክሸፍ የመከላከያ ሰራዊት ከአማራ እና አፋር ልዩ ኃይል ጋር በመጣመር ጥብቅ ቁጥጥር እያደረገ እንደሆነ ተገልጧል።
ከሰሞኑ የወጣው መረጃ እንደሚያሳየው ደግሞ፣ በአፋር ክልል በኩል ሾልከው ካገር ለመውጣት ጥረት እያደረጉ እንደሆነ ያመላክታል። የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እንዳለው፣ ተፈላጊዎቹ ‹‹የጁንታው›› ወንጀለኞች በአፋር ክልል ሾልከው የሚወጡበት ምንም አይነት ክፍተት እንደማይኖር ገልጧል።
Be the first to comment