ሕወሓት ምን ላይ ነው? | ዐቢይ ጉዳይ

ዕለተ ሰኞ ሰኔ 21/2013 የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ-ስፈጻሚ አብርሃም በላይ (ዶ/ር) የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጥያቄ ማቅረባቸው ተገለጸ። በጥቂት ሰዓታት ውስጥ የፌደራል መንግሥቱ አውንታዊ ምላሽ ሰጥቶ፤ የተናጠል የተኩስ አቁም ውሳኔ ላይ መድረሱን ይፋ አደረገ። በዚሁ ዕለት አመሻሽ ላይ የትግራይ ታጣቂዎች (እነሱ “TDF” የሚሉት) ከመቀሌ ሸሽተው ከወጡ ልክ በስምንተኛ ወራቸው ተመልሰው ከተማዋን ተቆጣጠሩ። ይህን ትዕይንት አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ ትራጀዲ በሆነ ዘውግ ሲመለከተው፤ ሕወሓትና ደጋፊዎቹ ደግሞ በ‹ውፈር ተበገስ› አጅበው የተረኩት አድቬንቸራቸው ነበር።

በዚህም ተባለ በዚያ፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ትግራይን ለቅቆ የወጣው በሕዝብ ተወግቶ ስለመሆኑ ታሪክ በጥቁር መዝገቡ ከትቦታል። አሸባሪው ሕወሓት በስምንት ወር የጫካ ቆይታው ሦስት ኃይሎችን ሚና አከፋፍሎ በመስጠት እንደተጠቀመባቸው መረጃዎች ያመለክታሉ። አንደኛ፣ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ውስጥ አስርጎ ያስገባቸው አባላቱን (ለመረጃና የእርዳታ እህል ለማጋዝ)፤ ሁለተኛ፣ ዓለም ዐቀፍ የተራድዖ ድርጅቶችን (ለፕሮፖጋንዳና ለቴክኖሎጂ ድጋፍ)፤ ሦስተኛ፣ በትግራይ የሚገኙ የሃይማኖት አባቶችን (የተንቤኑ ሕዝባዊ ማዕበል ከመጀመሩ ቀደም ብሎ ከበረሃ ወደ ከተማ አደረጃጀት ለመዘርጋት የሃይማኖት አባቶችን እንደ ንስሃ አባት ቤት ለቤት እያዞረ) ተጠቅሞባቸዋል።

የእነዚህ ሦስት ኃይሎች ቅንጅት በረሃ አብረውት ከወረዱ ታጣቂዎችና አዲስ ምልምል ወጣቶች ጋር አቀናጅቶ ሠራዊቱን ለማጥቃት ችሏል። የዚህ ቅንጅት ውጤት ነበር፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ እንደ ሕዝብ ጥቃት እንዲከፈትበት ያደረገው። ሕወሓት ጦሩን በአርሚ፣ በኮር እና በክፍለ ጦር ለማደረጃት የቻለው በዚህ መንገድ ነበር። እርግጥ ነው በመከላከያ ሠራዊት ውስጥ በገንዘብ የገዛቸው ከዳተኛ የጦር መኮንኖች የፈጠሩለትን ‹ሳቦታጅ› እንደ ዕድል ተጠቅሞበታል። በሰኔ ወር አጋማሽ የተካሄደው የተንቤኑ ውጊያ የእነዚህ ድምር ውጤት ነበር። በርግጥ ዘግይተው የወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት መቀሌ ከተማ ሰፍሮ የነበረው አራት ክፍለ ጦር በፍጥነት ባይወጣ ኑሮ፣ በሕዝባዊ ማዕበል የጥቅምት 24 የሰሜን ዕዝ ሰማዕታት ዕጣ ይገጥመው ነበር።

ይህም ሁኖ፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ከትግራይ ሲወጣ ከግምት በላይ የሆነ ሰብዓዊና ቁሳዊ ጉዳት ደርሶበታል። ‹ወደ ሕዝብ አንተኩስም› ያሉ ባለመለዮዎች በክብር ራሳቸውን ሰውተዋል። በሕዝብ ማዕበል ከበባ ውስጥ ገብተው በድምጽ አልባ መሳሪያ የተጨፈጨፉ በርካቶች ናቸው። ዕድለኞች ከሆን የወቅቱ ዘማች የሠራዊቱ አባላት ወደፊት ስለሰሜኑ ጦርነት ግለ- ታሪካቸውን ከፃፉ ሁነቱን ያስነብቡን ይሆናል።

 Continue reading

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*