እስክንድርን የደበደበው ማነው?

ሰሞኑን በእስር ላይ የሚገኙት የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ሊቀመንበር አቶ እስክንድር ነጋ ላይ ማረሚያ ቤት ውስጥ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ተሰምቷል። አቶ እስክንድር በተፈፀመባቸው ድብደባ ጉልበታቸው፣ ግንባራቸው እና ዐይናቸው አካባቢ ጉዳት እንደደረሰባቸው ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ በመግለጫው አስታውቋል።

አቶ እስክንድር ሰሞኑን ፍ/ቤት ለመቅረብ ቀጠሮ የነበራቸው ቢሆንም፤ ሳይቀርቡ መቅረታቸውን ፓርቲው ጠቀሶ፤ «በተከታታይ ምስክር የመስማት ቀጠሮ ተሰርዞ፤ ለጥቅምት 15/2014 ዓ.ም ተዘዋውሯል» ብሏል። በተያያዘም ችሎቱን ለመታደም የተገኙ ሰዎች በጅምላ ታፍሰው ልደታ ፖሊስ ጣቢያ መም ሪያ መወሰዳቸውን አስታውቋል።

የድምፃዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ፣ በአዲስ አበባ ከተማ ተፈጥሮ በነበረው ሁከት እና ብጥብጥ በደረሰው የሰዎች ሞት እና የንብረት ውድመት ጋር በተያያዘ ክስ በተመሰረተባቸው የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አመራሮች፡- እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ አስቴር ሥዩም እና አስካለ ደምሌ ላይ የተለያየ ፖለቲካዊ በደል እየተፈፀመ መሆኑን ጉዳዩን ተንተርሰው የወጡ መረጃዎች ያመላክታሉ።

በመረጃው ላይ መረዳት እንደሚቻለው፣ አቶ እስክንድር ተደጋጋሚ ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል። በርግጥም፣ በእስር ቤት የሕግ ጥላ ሥር ሆኖ እንዲህ ዐይነት ድብደባ መፈፀሙ ብዙዎችን ያሳዘነ ጉዳይ ነው። ድርጊቱ ሕግን ያልተከተለ ተግባር ከመሆኑም በላይ የአገሪቱን የፍትሕ ሁኔታ የበለጠ ሥጋት ውስጥ የሚከት መሆኑ አይዘነጋም።

Continue reading

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*