የ’ዘር ማጥፋቱ’ ተጨማሪ ማሳያዎች

ሞኑን በኦሮሚያ ክልል ሆሮጉድሩ ወለጋ ዞን የተለያዩ አካባቢዎች የተፈፀመው ግድያ ብዙዎችን አሳዝኗል። ግድያው የዐማራ ክልል ተወላጆችን ዋነኛ ዒላማ ያደረገ መሆኑን ከስፍራው ለዝግጅት ክፍላችን የደረሰው መረጃ ያመላክታል። የሰሞኑን ጨምሮ በተለያየ ጊዜያት በአካባቢው የሚኖሩ ዐማራዎች ላይ የተፈፀመው የጭካኔ ግድያ የዘር ማጥፋት ማሳያ ነው ተብሏል።

በመሆኑም ከባለፈው የካቲት 27/2013 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ባለፈው ሳምንት ድረስ በተፈፀመው ዘር ተኮር ጥቃት፤ ቢያንስ ከ60 በላይ የሚገመቱ ዐማራዎች በማንነታቸው ተለይተው በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው ታውቋል። ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ህፃናት ደግሞ ወንዝ አካባቢ ሞተው ሲገኙ፤ በታጣቂዎች ታግተው ወደ ጫካ የተወሰዱ በርካታ ሰዎች መኖራቸውም ተጠቁሟል።

ይህ ዜና ተጠናቅሮ ወደ ማተሚያ ቤት እስከገባበት ዕለት ድረስ በአካባቢው ያለው ግድያ አልቆመም ነበር። ስለዚህም የሟቾችም ሆነ የቁስለኞች እንዲሁም የተፈናቃዮች ቁጥር ይጨምራል ተብሎ ይገመታል። የፀጥታው ሁኔታ አስቸጋሪ ከመሆኑ አኳያ የተገደሉት ሰዎች አስከሬናቸው በወቅቱ ሳይነሳ ቆይቷል። ከዚህ በፊትም ሆነ በአሁኑ ወቅት እየተፈጸመ ያለው ጥቃት የዐማራ ተወላጆች በብዛት ይኖሩበታል ተብሎ በሚታሰብባቸው የወለጋ አካባቢዎች ነው ተብሏል።

እንደ አካባቢው ኑዋሪዎች ጥቆማ ግድያውን በዋናነት የሚፈጽመው ‹‹ኦነግ-ሼኔ ነው›› ይባል እንጂ፤ የክልሉ መንግሥት ያሰማራቸው ልዩ ኃይሎች እና አንዳንድ የመንግሥት ኃላፊዎች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለታጣቂ ቡድኑ መረጃ ከማቀበል ጀምሮ ተባባሪ መሆናቸውን ይናገራሉ። በጉዳዩ ላይ ግልፅ መረጃ ለህዝብ ከመስጠት ይልቅ በማስተባበያ እና በማለባበስ በሚያልፉት የመንግሥት ተወካዮች ምክንያት ችግሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መምጣቱም አያይዘው ይጠቅሳሉ።

Continue reading

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*