ድሬዳዋን ‹የማዳን› ምርጫ

ንቦት 28 እና ሰኔ 5/2013 ዓ.ም ድምፅ የሚሰጥበት ስድስተኛው አገር ዐቀፍ ምርጫ፣ ከአንድ ወር ያነሰ ጊዜ ቀርቶታል። ከሌሎች ክልሎች አንድ ሳምንት ዘግይቶ ድምጽ የሚሰጥባቸው የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተማ መስተዳድሮችን የምርጫ ቀን በተመለከተ የተላላፈው ውሳኔ አወዛጋቢነት ዛሬም ድረስ እንደቀጠለ ይታወቃል። በወቅቱ አንዳንድ ፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ‹ውሳኔው ትክክል ስላልሆነ የሌሎች ክልሎች ምርጫ በሚካሄድበት ዕለት እንዲደረግ ቢጠይቁም፤ ምርጫ ቦርድ በውሳኔው ፀንቷል። ከሰሞኑ የወጣ መረጃ እንደሚጠቁመው ደግሞ፣ ሦስት የፖለቲካ ፓርቲዎች (ባልደራስ፣ እናት እና አብን) የምርጫው ቀን በተመሳሳይ ዕለት እንዲደረግ የሚጠይቅ ደብዳቤ ለቦርዱ ማስገባታቸውን “አዲስ ማለዳ ጋዜጣ” በሚያዚያ 30/2013 ዓ.ም እትሟ አስነብባለች። ይህን ተከትሎ ምርጫ ቦርድ ውሳኔውን በቅርብ እንደሚያሳውቅ ተናግሯል።

የሁለቱ ከተማ መስተዳድሮች ምርጫ፣ ከሌሎች አካባቢዎች አንድ ሳምንት ዘግይቶ እንዲደረግ መወሰኑ ጥያቄ ካስነሳበት ምክንያቶች ውስጥ ዋንኞቹ፣ በአስተዳድሮቹ ያለው ፖለቲካዊ ሥርዐት ሕዝብን አሳታፊ ባለመሆኑ እና ከፍተኛ የህልውና አደጋ ያንዣበበባቸው ከተሞች በመሆናቸው እንደሆነ ይጠቀሳል። በተለይ “40 40 20” በሚባል ያልተፃፈ አስተዳደራዊ መዋቅር የተደቆሰችው የምስራቋ ከተማ ድሬዳዋ፣ ላለፉት ዐመታት የቆየችበት የሞግዚት አስተዳደር ነዋሪዎቿን ለከፋ አስተዳደራዊ ብልሹነት አጋልጧል። የከተማዋን ወጣቶችም ሥራ በመንፈግ፣ በአገሪቱ ከፍተኛ የሥራ-አጥ ቁጥር የተከማቸባት ከተማ እንድትሆን አድርጓል። ከዚህ በተጨማሪ፣ ለህልውናዋ መዳከም፣ ለፍትሕ እጦት፣ ለከፋ ማኅበራዊ ምስቅልቅሎሽ የመጋለጧ ሁሉ መነሾ ነው።

በዘጠኝ የከተማ ቀበሌዎች እና በሠላሳ ስምንት የገጠር ቀበሌዎች በቻርተር ደረጃ የተመሰረተችው ድሬደዋ፣ ከ1987 እስከ 1995 ዓ.ም ድረስ በአዋጅ ቁጥር 7/1984 ‹‹ጊዜያዊ አስተዳደር›› በሚል በፌዴራል መንግሥቱ ስር እንደነበረች ይታወሳል። በዚህም እስከ 1995 ዓ.ም ከፌዴራል መንግሥቱ በሚሾምላት ሊቀ-መንበር ስትመራ ቆይታለች።

Continue Reading

 

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*