ሊታረሙ የሚገባቸው የቅድመ-ምርጫ ሁኔታዎች – ርዕዮት አለሙ

ኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ፣ ወቅቱ የምረጡኝ ቅስቀሳ ወይም የምርጫ ዘመቻ የሚካሄደበት መሆኑ ይታወቃል። በዚህ መሰረት የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ማኒፌስቷቸውን እና የመወዳደርያ ምልክታቸውን ይፋ ማድረግ ጀምረዋል። በየአደባባዩም የምርጫ ቅስቀሳዎችን እያደረጉ ነው። ቅስቀሳቸውንም ካለፉት የምርጫ ጊዜዎች በተለየ መንገድ ሲያደርጉ ተስተውሏል። ያለ ክፍያ የሚገባባቸው የሙዚቃ ኮንሰርቶች እና በነፃ አገልግሎት የሚሰጡ አውቶብሶችን በማቅረብ ጭምር፣ ቅስቀሳውን እያጧጧፉት ነው። በሌላ በኩል ገና ካሁኑ ምርጫው ፍትሐዊ እና ሰላማዊ ሆኖ የመጠናቀቁ ሂደት ላይ፣ ጥያቄ ሊያስነሱ የሚችሉ መጥፎ አዝማሚያዎች መታየታቸው አልቀረም።

ከእነዚህ አዝማሚያዎች ውስጥ ገለልተኛ ሊሆኑ የሚገባቸው ተቋማት አድሏዊ እና ችግር ፈጣሪ ሆነው መገኘታቸው ተጠቃሽ ነው። ለምሳሌ ባለፈው እሁድ ተደርጎ የነበረውን የባልደራስ፣ የዐብን፣ የመኢአድ እና የኢብአፓ የጋራ የምርጫ ማስጀመርያ መርሀ-ግብርን፣ ሁለት የመንግሥት ሚዲያዎች እንዴት እንደዘገቡት መመልከት እንችላለን። የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽንን እናስቀድም፡- “ዐብን በአዲስ አበባ የምርጫ ቅስቀሳ ማስጀመርያ መርሀ-ግብር አካሄደ። ፓርቲው የምርጫ ቅስቀሳ ማስጀመርያ መርሀ-ግብሩን አብሮ ለመሥራት ከተስማማቸው ፓርቲዎች ጋር በጋራ አከናውኗል፤” በማለት ነበር የዘገበው። ኢቢሲ የፈፀመው ቀና ስህተት ላለመሆኑ አስረጂው ደግሞ፣ በፌስቡክ ገፁ የለጠፋቸው ሰባት ፎቶዎች ናቸው። ….

Continue reading

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*