‹‹ሕዝቡ ድምፁን እንዲጠብቅ እናነቃለን›› በለጠ ሞላ (ረዳት ፕሮፌሰር)

የ “ዐማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (ዐብን)፣ የፊታችን ግንቦት የሚደረገውን አገር ዐቀፍ ምርጫ በተመለከተ ያደረገው ግምገማ፣ ትንተና እና በአጠቃላይ የደረሰበት አቋም ምን ይመስላል?

ኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ምስቅልቅል ውስጥ ያለች አገር መሆኗ የሚካድ አይደለም። ሰዎች በማንነታቸው ብቻ ከተለያዩ ክልሎች ተገፍውና ተፈናቅለው ድንኳን ውስጥ ተጠልለው ይገኛሉ። በየጎዳናው የወደቁም አሉ። ትግራይ ውስጥ ‹‹የሕግ ማስከበሩ›› ሥራ ገና መቋጫ አላገኘም። የአገራችን ሉዓላዊነትና ዳር-ድንበር በሱዳን ተደፍሯል። በኦሮሚያ ክልል በወለጋ የታጣቂዎችን እንቅስቃሴ እና በቤንሻንጉል መተከል ዞንን ጨምሮ፤ በኢትዮጵያ ሰፊ ቦታዎች ዜጎች ላይ የህይወት አደጋ የጋረጡ፣ የመኖር ህልውናቸውን የፈተኑ አያሌ ችግሮች አሉ። እነዚህ ሁኔታዎች ጊዜው ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና ነፃ ምርጫ ለማካሄድ ምቹ አይደለም ወደሚል መላምት መውሰዳቸው አይቀርም።

የሆነው ሆኖ፣ ይህ መንግሥት ሕዝባዊ ቅቡልነት ያለው ካለመሆኑ አኳያ እና ‹ምርጫ ይደረጋል› ብሎ ከመዘጋጀቱ አንፃር፤ ሕብረተሰቡ በምርጫው ተሳትፎ፣ ይመራኛል ብሎ ያመነበትን መንግሥት መመስረት አለበት። እኛም ባለፈው እሁድ የምርጫ ቅስቀሳ በይፋ ማስጀመሪያ የአደባባይ ትዕይንት አድርገናል። ይህም ጥሩ መነቃቃት ፈጥሯል ብለን አንናምናለን።

የጠራችሁት ሰልፍ ቀዝቃዛ ነበር ይባላል? ……..

Read More

 

 

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*