“አንዳንድ ሕዝቦች ራሳቸውን ከኢትዮጵያ ነጥለው እንዲያስቡ ያልተደረገ ጥረት የለም” – ዲያቆን ዳንኤል ክብረት (የግል ተወደዳሪ)

መንፈሳዊ አገልግሎት ላይ ያሉ ሰዎች ወደ ፖለቲካው መድረክ መምጣታቸውን በበጎ የማይመለከቱ አሉ:: የአንተ ሀሳብ ምንድ ነው? ወደ ፖለቲካ እንድትገባ ያደረገህ ገፊ-ምክንያትስ ምንድን ነው?

ዓለማውያን ይግቡ፣ መንፈሳውያን ይቅርባቸው፤ መንግሥትን ወይም የግል ድርጅትን ሲያገለግሉ የነበሩ ፓርላማ ይግቡ፣ ቤተ-ክርስቲያንን ወይም መስጊድን ሲያገለግሉ የነበሩ ይቅርባቸው የሚል ሕግና ደንብ ያወጣው ማነው? የየትኛውስ አገር ልምድ ነው ይሄንን የነገረን? በበጎ አለመመለከት መብታቸው ቢሆንም፤ በበጎ ያልተመለከቱበት መንገድ ግን አሳማኝ አይደለም። ‹ከሚቀር እንናገር፣ ከምንተወው እንሠንዝር› ብለው ያመጡት ነው።

ኢትዮጵያ አሁን የገጠማትን አጣብቂኝ ለማለፍ እንድትችል የሁላችንም ሚና ያስፈልጋታል። መጭው ዘመን የኢትዮጵያና ማኅበረ ፖለቲካዊ መዋቅር የሚቀይር ነው። ይሄንን ዘመን ከደለደልነው፣ ቀሪው የአገሪቱ ዘመን የተደላደለ ይሆናል። የዳር ተመልካች ሆነን ካየነው ግን የማንን ቤት ማን ያቃናልናል? ለዚህ ነው የገባሁት።

የምርጫ ቅስቀሳህ መሪ ቃልህ “ኢትዮጵያዊነት በርቱአዊነት” የሚል ነው፤ በዋናነት ልታስተላልፍ የፈለከው መልዕክት ምንድን ነው?

Continue reading

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*