“ኦነግ ከግለሰብም በላይ ነው” – የኦነግ ቃል-አቀባይ ኦቦ ቀጀላ መርዳሳ

ኦነግ በምርጫው ላይ የያዘው አጠቃላይ አቋም ምን ይመስላል?

በ2010 ዓ.ም የመጣውን ለውጥ ተከትሎ፣ ለሁለት ዐመት ተኩል አካባቢ ‹ምርጫው ምህዳሩ በሰፋ የዴሞክራሲ ሂደት ይከናወናል› ተብሎ ተስፋ ተጥሎበት ነበር። በኋላ ግን ችግሮች፣ እንቅፋቶች፣ መደነቃቀፎችና ግጭቶች ተበራክተዋል። አምና በ2012 ዓ.ም ለምርጫ በተዘጋጀንበት ጊዜ ደግሞ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መጣና ሁኔታውን በይበልጥ አወሳሰበው። የአርቲስት ሀጫሉ ሀንዴ ግድያን ተከትሎም ብዙ ቀውስ፣ ሕገ-ወጥነትና አለመረጋጋት መበራከቱ፣ በምርጫው ላይ ጥሩ ያልሆነ ድባብ ጥሏል።

የሆነ ሆኖ፣ ‹በዚህ ዐመት ምርጫ ይደረግ ሲባል› የእኛ ፓርቲ ቅድም በጠቀስኩት ምክንያቶች ዝግጅት ካለማድረጉ በተጨማሪ፤ የውስጥ ችግራችን፣ ማለትም በሊቀ-መንበሩ [ዳውድ ኢብሳ] እና በሌሎች አመራሮች መካከል በተፈጠረው ውጥረት የተነሳ፣ በዋናነት በውስጥ ጉዳያችን እንድንያዝ፣ ወደፊት እንዳንራመድና ስለምርጫው እንዳናስብ አድርጎናል።

በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያለን ነው እንግዲህ የምርጫው ጊዜ የተቃረበው።

በኦሮሚያ ምን ያህል ቢሮ ተዘግቶባችኋል? የታሰሩባችሁ አባላቶችስ አሉ?

በኦሮሚያ ብዙ ቢሮዎች ተከፍተው ነበር። እኛ ‹በዚህ አካባቢ›፣ ‹እዛ አከባቢ› ብለን በጀት ይዘን፣ እቅድ ይዘን ቢሮዎችን አልከፈትንም። ቢሮዎቹን የከፈቱልን ደጋፊዎቻችንና የአካባቢው ህብረተሰብ በራሳቸው ተነሳሽነት ነው። ያም ሆኖ አሁን ላይ የተዘጉ ቢሮዎች ብዙ ናቸው። የተዘጉባቸው ምክንያቶችም ይለያያሉ። ከእነዚህ ውስጥ የቤት ኪራይ ባለመክፈል፣ ቋሚ ሠራተኞች ባለመቅጠር እና በአስተዳደራዊ ችግር የተዘጉ አሉ። ሌላው በአንዳንድ አካባቢዎች ግጭት ሲፈጠር በፍርሃት ወደ ቢሮ ለመሄድ አለመፈለግ ነው። ነቀምት ላይ ደግሞ በአባላት መካከል አለመግባባት በመፈጠሩ፤ እንዲሁም በመንግሥት እና በኦነግ መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ለቢሮዎቻችን መዘጋት ተጠቃሽ ምክንያቶች ናቸው።

Continue reading

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*