የ’ሰኔ 14’ ቀጠሮ | ምስጋን ዝናቤ ተሜ

ዕለተ-ሰኞ፥ ሰኔ 14/2013 ዓ.ም ስኬታማ ምርጫ ከተካሄደ ለኢትዮጵያ የታሪክ መታጠፊያ የሚሆን ይመስለኛል። ከብዙ መዋዕለ-ነዋይ ፍሰትና የሰው ሕይወት ግብር በኋላ፣ የአገሪቱን መሪ በሃሳብ ብልጫ ለመወሰን ጊዜው ዕድልን ወይም በደልን ጥሎ ለማለፍ እየተጣደፈ ነው። ምኞቴ ግን፣ የሕዝብ ድምፅ ተከብሮ የዴሞክራሲ ፀሐይ መሞቅ ነው። ይህም ሆኖ፣ በትላንት ፖለቲካዊ በደል ውስጥ ዛሬን በጥርጣሬ መመልከቱ ተፈጥሯዊ ነው።

አምስቱ የብሔራዊ ምርጫ ታሪክ መጥፎ ትዝታ አለው። ‹‹ድምፅ ላይከበር፣ ድምፅ መስጠቱ ምን ዋጋ አለው?›› እስከ ማለት ይገፋፋል። አገዛዙ የዘጋው ማሰብን ወይም ተራማጅነትን እስከሆነ ድረስ፣ ያለ ሃሳብ ሥልጣኔ ዴሞክራሲን ማለም ቅዠት ሊሆን ይችላል። በበኩሌ፣ ስለ ዴሞክራሲ ጽንሰ-ሃሳብም ሆነ ሥርወ-ቃል አንብቤ የተረዳሁት ከግሪክ ፈላስፎች ጋር መመሳሰሉ አልቀረም። ለቃሉ የሰጡት ትርጉም እንዲህ ይላል፡-

‹‹ሰዎች ሃሳባቸውን በነፃነት የማንሸራሸር መብታቸውን የሚያውጁት በዴሞክራሲ ነው። ፖለቲካ ደግሞ በዴሞክራሲ ሥም የሚነግዱ ‹አፈ-ቀላጤዎችን› ወደ ሥልጣን ያመጣል። አብዛኛው ኅብረተሰብም ፖለቲከኞች ስለሚናገሩት እንጂ፣ ስለሚተገብሩት ፖሊሲ የማመዛዘን ልምድ አላዳበረም። ስለዚህ፣ ፖለቲካ ሥርዐትን ባልመረመሩ መራጮች የተነሳ አገርና ወገን የሚበድሉ አመራሮችን ወደ ሥልጣን የማውጣት ዕድሉን ያሰፋል።››

Continue reading 

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*