“የሶማሌ ሕዝብ ከጎሰኝነት ይልቅ፣ በሀሳብ ያምናል” – አሕመድ መሐመድ (የኦብነግ የፌደራልና ዲፕሎማቲክ ጉዳዮች ኃላፊ)

“ኦብነግ እርስ-በርሱ ተከፋፈለ” ሲባል ሰምቼ ነበር። ችግሩ ምንድን ነው? አሁንስ ተፈቷል?

እንደ ሰው ልጅ የሀሳብ ልዩነት ይኖራል። ይህ ደግሞ ነውር አይደለም። የሀሳብ ልዩነት ለሥራ ጥሩ ነው። ሥራ እስካለ ድረስም የሀሳብ ልዩነት ይኖራል፣ አያልቅም። እኛ ልዩነቱን እንደ እንቅፋት አናየውም።

የሶማሌ ክልል መንግሥት የፖለቲካ ምህዳሩን እያጠበበው እንደሆነ ቅሬታ ይቀርብበታል። እናንተስ ምን ትላላችሁ?

ከገዢው ፓርቲ ብዙ ጫናዎች አሉብን። ግማሹን እጩዎቻችንን እንኳን ማስመዝገብ የቻልነው በትልልቅ አካባቢዎች እንደ ጅጅጋ ቀብሪ ድሀር፣ ደገሀቡር ያሉ ቦታዎች ላይ ነው። ዳር ዳር ያሉ አካባቢዎች ላይ እጩ ማስመዝገብ አልቻልንም። አባሎቻችን ተደብድበዋል፣ ታስረዋል። በዚህ ምክንያት ከ100 በላይ የሚሆኑ እጩዎችን አዲስ አበባ ባለው ምርጫ ቦርድ ነው ያስመዘገብነው። መራጮችንስ አዲስ አበባ ነው የምናስመዘግባቸው? ወይስ እንዴት ይሆናል? ለሚለው እስከ አሁን መልስ አላገኘንለትም።

የክልሉ አመራሮችም ‹ባለን ዐቅም ኦብነግን ማጥፋት አለብን› ብለዋል። ለዚህም በቂ ማስረጃ ልናቀርብ እንችላለን። ሙስጠፋ ታዛዥ ነው። ብቻውን አንድ ነገር ሊያደርግ እንደማይችልም እናውቃለን።

ለክልሉ ምክር ቤት እና ለፌደራሉ ምን ያህል እጩዎችን አቅርባችኋል?

Continue reading

 

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*