በልዩ ኃይሎች ላይ ያልተማመኑ ዜጎች

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የክልል ልዩ ኃይሎች የፀጥታ ችግሮችን ከማረጋጋት ይልቅ፣ ለማባባስ ምክንያት መሆናቸውን የሚጠቁሙ መረጃዎች ከየአካባቢው ይወጣሉ። በትንሹ የጀመረውን የግለሰቦች ጠብ ወደ ከፋ የእርስበርስ ግጭትና ሞት ይመሩታል የተባሉት አንዳንድ የልዩ ኃይል አባላት ወደ ኑዋሪዎች በመተኮስ ችግሩን ያሰፉታል ተብሏል። የፖለቲካ ተንታኞች የልዩ ኃይል አመሰራረት ከመጀመሪያው ጀምሮ ለአገር ጠቃሚ አለመሆኑን ይናገራሉ።

ዜጎችም በልዩ ኃይል ላይ ያላቸው እምነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሸረሸረ የመጣ መስሏል። ሰሞኑን በደቡብ ክልል፣ አርባ ምንጭ ከተማ የተከሰተው የፀጥታ ችግር በማሳያነት ተጠቅሷል። በክልሉ ልዩ ኃይል አባል ‹ተወሰደ› በተባለ እርምጃ፤ የአንድ ወጣት ሕይወት ማለፉ ተነግሯል። ሌላ ታዳጊ ልጅ ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት መድረሱ ታውቋል። ይህ ድርጊት የተፈፀመው በአርባ ምንጭ ሲቀላ ክፍለ ከተማ፣ በድል ፋና ቀበሌ በሚገኝ አንድ ግሮሰሪ ውስጥ ነው።

የፀጥታ ችግሩ መነሻ፣ በአካባቢው ወጣቶች መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ነው። በወቅቱ በግሮሰሪው ውስጥ የሲቪል ልብስ ለብሶ በመዝናናት ላይ የነበረ አንድ የክልሉ ልዩ ኃይል አባል እንደነበር ተጠቁሟል። የልዩ ኃይል አባሉ እርምጃውን የወሰደውም ወጣቶቹ ተሰብስበው ጉዳት ሊያደርሱበት ስለነበር ነው ተብሏል። ቡድን ፈጥረው ሊደበድቡት ሲሉ ራሱን ለመከላከል በተኮሰው ጥይት አንድ ሰው ተመትቷል።

Continue reading

 

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*