የሕዝበ-ውሳኔው ጉዳይ

ኢሕአዴግ ፖለቲካዊ መዋቅር እስካሁን ለሚፈፀሙ ችግሮች መሰረት ነው። ዜጎች በገዛ አገራቸው ተሳዳጅ ሆነው ቆይተዋል። የነበረው የጋራ እሴት ፈራርሶ ለዘረኛው ፖለቲካ ተገዢ እስከመሆን ወይም አንዳቸው ለሌላቸው የነበራቸው የመከባበር ባሕልን አደብዝዞታል። ማንኛውም ጉዳይ ከብሔር እና ከእምነት አኳያ እየተለካ ሰብዓዊነት እየጠፋ መጥቷል።

በዚህ የዘውግ አወቃቀር ከመሰረታቸው ክልሎች ውስጥ ደቡብ ክልል አንዱ ነው። ክልሉ የተዋቀረበት መንገድ ከሌሎቹ የአገሪቱ አካባቢዎች የተለየ እና ጥያቄ የሚነሳበት ነው። አወቃቀሩ በክልሉ ብዙ ባህል እና ቋንቋ ያላቸውን የማኅበረሰብ ክፍሎች በኢኮኖሚያዊ እና አስተዳደራዊ ተጠቃሚነት እንዲገለሉ መንስኤ ሆኗል። ይህም በክልሉ የአደረጃጀት እና የመልማት ጥያቄዎች ከሌላው የሀገሪቱ ክፍል በስፋት እንዲነሳበት አድርጓል።

በተለይም ከ2010 ዓ.ም ለውጥ በኋላ በክልሉ የአደረጃጀት ጥያቄዎች ጎልተው መነሳት ጀምረዋል። ከነዚህም በዋናነት ገዝፎ የሚነሳው የሲዳማ ህዝብ ክልል የመሆን ጥያቄ ነው። ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ ለረጅም አመታት ሲያነሳ የቆየው የሲዳማ ህዝብ፣ ጥያቄው ባለፉት ሁለት አመታት መልስ አግኝቶ በህዝበ ውሳኔ ከደቡብ ክልል ተነጥሎ ራሱን የቻለ ክልል ለመሆን በቅቷል። ከሲዳማ ህዝብ በተጨማሪም የወላይታ፣ የጉማይዴ፣ የኮንሶ፣ የከፋ፣ ዳውሮ፣ ኮንታ ሌሎችም በክልሉ ያሉ ህዝቦች ከወረዳነት እስከ ክልልነት ጥያቄ ያነሳሉ።

Continue reading

 

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*