
የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በሀገር ደረጃ እየተባባሰ መምጣቱ የጤና ሚንስቴር የሚያወጣው መረጃ ጠቋሚ ነው። የወረርሽኙ መስፋፋት በተለይም በከተሞች አካባቢ እንደሚስተዋል ይነገራል። ድሬዳዋ ደግሞ በከተማ ደረጃ ኮሮና ቫይረስ በስፋት እንደሚታይባት ተገልጿል።
ወረርሽኙን በሀገር ደረጃ አሳሳቢ ያደረገው ምክንያት የታማሚዎች ቁጥር ከመተንፈሻ መሳሪያ ጋር አለመጣጣሙ ነው። በዚህ ሳቢያ ህክምና የሚሹ ሰዎች በህክምና ተቋማት እንዲቆዩና ክትትል እንዲደረግላቸው አለመቻሉም በህክምና ባለሞያዎች በተደጋጋሚ ይናገራሉ።
በተመሳሳይ በድሬዳዋም ወረርሽኙ መስፋፋቱን ተከትሎ የመተንፈሻ መሳሪያዎች ዕጥረት ይስተዋላል። የከተማ ጤና ቢሮ የኮቪድ-19 ህክምና ማዕከል ሆኖ እያገለገለ የሚገኘው የፈረንሳይ ሆስፒታል ክሮምቶ ማኑፋክቸሪንግ ፒልሲ 50 ኦክስጂን የተሞላባቸውን ሲሊንደሮች በድጋፍ መልክ በማበርከት ችግሩን አቅልሎታል።
Be the first to comment