ከቁጥጥር ውጪ የሆነው የተፈጥሮ አደጋ

በድሬዳዋ ከተማ ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ እየጣለ ያለው ዝናብ በሰው ህይወት እና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ነው። እስካሁን ባለው መረጃ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን፤ በንብረት ላይም ጉዳት ደርሷል። በየወቅቱ በአስተዳደሩና በአጎራባች የኦሮሚያ ወረዳዎች በሚዘንበው ዝናብና በሚፈጠረው ደራሽ ጎርፍ ሳቢያ፣ በተለያዩ ጊዜያት በሰዎች ላይ የሞት፣ በንብረት ላይ ውድመት፣ እንዲሁም በእለት ተእለት የህብረተሰቡ የአኗኗር ሂደት ላይ ጉዳት ሲያስከትል መቆየቱ ተነግሯል።

ባለፉት ሳምንታት በከተማ የዘነበው ዝናብ፣ ለጎርፍ መከሰት ምቹ ሁኔታን በመፍጠሩ፣ በከተማ እና በገጠር አካባቢዎች የጎርፍና ተያያዥ አደጋዎች ተከስተዋል። በዚህም ምክንያት ከብሔራዊ ሜትሮሎጂ ኤጀንሲ፣ በቀጣይ ጎርፍ ሊከሰት እንደሚችል ለነዋሪዎች የጥንቃቄ መልዕክት ተላልፎ ነበር። በተላለፈው የቅድመ ማስተንቀቂያ መረጃ መሠረት ሊደርስ የሚችለውን አደጋ በእጅጉ ለመቀነስ እንደተቻለ አስታውቋል።

በከተማው ረቡዕ ሚያዝያ 27 ቀን 2013 ዓ.ም ምሽት ጀምሮ በጣለው ከባድ ዝናብ የአንድ መኖሪያ ቤት አጥር ግንብ ፈርሶ በመኖሪያ ቤት ላይ በመውደቁ የሶስት ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን፣ አንድ ሰው በመብረቅ አደጋ ህይወቱ ማለፉ ተነግሯል። እንዲሁም በቀበሌ 08 ልዩ ስሙ “ለገሃሬ ከመንገድ በላይ” ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከለሊቱ ዘጠኝ ሰአት ጀምሮ በጣለው ከባድ ዝናብ የአንድ መኖሪያ ቤት አጥር ተደርምሶ በአቅራቢያው ባለው መኖሪያ ቤት ላይ በመውደቁ በቤቱ ውስጥ ተኝተው የነበሩ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ 3 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

Continue Reading 

 

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*