የዘጠኝ ፓርቲዎች ጥምረት

በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ለ6ኛው አገር አቀፍ ጠቅላላ ምርጫ ህጋዊ እውቅና አግኝተው የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፖርቲዎች የጋራ መድረክ ምስረታ አካሂደዋል። በመድረኩ ዘጠኝ ፖርቲዎች የተሳተፈ ሲሆን የጋራ መግባቢያ የቃል ኪዳን ሰነድ ተፈራርመዋል።

በፖለቲካ ፖርቲዎቹ መካከል የጋራ መድረክ መመስረቱ በተፎካካሪ ፖርቲዎች መካከል በመተማመን ላይ የተመሰረተ ዲሞክራሲያዊ ውይይት እንዲኖር ያስችላል ተብሏል። እንዲሁም በመደማመጥና በመከባበር ላይ የተመሰረተ ምክንያታዊ ውይይት እንዲኖር ይረዳል የሚል ሀሳብ ተነስቷል።

ሌላኛው የፓርቲዎቹ የጋራ መድረክ መፍጠር ጥቅም፣ የአገራዊ ጥቅምን ቅድሚያ መስጠትን፣ የህዝብን ጥቅም ማስቀደም እና መሰረታዊ የሆኑ የሰብዓዊና የእኩልነት መርሆዎችን የተከተለ የጋራ የምክክር መድረክ በዘላቂነት እንዲኖር ለማስቻል ይረዳል። በተጨማሪም በቀጣይ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ለማካሄድ እና የፖለቲካ ፖርቲዎች የሚዲያ አጠቃቀምን ህግንና ስርአትን የተከተለ ለማድረግ ስምምነቱ ያግዛል መባሉን መረጃዎች ይጠቁማሉ።

Continue reading

 

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*