አረንጓዴ አሻራ

2010 ዓ.ም ጀምሮ በስፋት እየተተገበረ ያለው የአረንጓዴ ልማት አሻራ፤ ለኢትዮጵያ ተስፋ ሰጪ ለውጦችን እያመጣ እንደሆነ ይነገራል። በተለይም ዓለምን እየፈተነ የሚገኘው የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የሚደረገውን እንቅስቃሴ በጉልህ አግዞታል። የፓሪሱን የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት ተቀብላ እየተገበረች ያለችው ኢትዮጵያ፣ ባለፉት ሁለት ዐመታት አረንጓዴ ልማት ላይ በሰጠችው ትኩረት የደን ሽፋኗን ማሳደግ ችላለች።

በዘንድሮውም ዓመት ተጠናክሮ የሚቀጥለው የአረንጓዴ ልማት አሻራ ፕሮግራም የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ ነው። በጋምቤላ ክልል በዘንድሮው ክረምት የሚተገበረውን የአረንጓዴ ልማት አሻራ መርሃ ግብር ለማሳካት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ የጋምቤላ ክልል የእርሻ እና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢጁሉ ሉዋል ገልፀዋል።

እንደ ቢሮው ኃላፊ ገለፃ ከሆነ፣ በ2013 ዓ.ም የሚተገበረውን የአረንጓዴ ልማት አሻራ ንቅናቄ የተሳካ ለማድረግ እስካሁን ባለው ሂደት አራት ሚሊዮን የዛፍ ችግኞች ዝግጁ ሆነዋል ብለዋል።እንዲሁም ቀሪዎቹን ችግኞች ለታለመለት አላማ ለማድረስ ርብርብ እየተደረገ እንዳለ ኃላፊው አያይዘው ገልጸዋል።

Continue reading

 

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*