
በአብዛኛው የማኅበረሰብ ክፍል ዘንድ እየተዘነጋ የመጣው የኮሮና ቫይረስ ዛሬም ሰው እየገደለ፣ ኢኮኖሚ እያቃወሰ፣ የዜጎችንም ማኅበራዊ ሕይወት እያወሳሰበው መሆኑ ይታወቃል። የሰለጠኑ አገራት እንኳን ቫይረሱን ለመከላከል አቅም አጥተው በተለያየ የችግር ደረጃ ውስጥ ይገኛሉ። ቫይረሱም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፋ እንጂ እየቀነሰ አለመምጣቱ ስለመምጣቱ እየተዘገበ ነው። በዚህም አገራት በቫይረሱ እየተፈታተኑ ነው።
ኢትዮጵያ ከገጠማት የፀጥታ ችግር ጎንለጎን የኮሮና ወረርሽኝ በእጅጉ እየፈተናት መሆኑ አይዘነጋም። በተለያየ ጊዜያት የተፈናቀሉ ዜጎቿም የቫይረሱ ተጠቂ ይሆናሉ የሚል ሥጋት ፈጥሯል። ሰዎች በሚሰበሰቡበት ወቅት ይበልጥ የሚስፋፋው ቫይረስ ከጥንቃቄ ጎድለት ጋር ተዳምሮ ጉዳት እያደረሰ ነው።
በአጠቃላይ ኢትዮጵያ የዜጎቿ በቫይረሱ መሞት የሰው ኃይል እያሳጣት መሆኑ አይዘነጋም። የአገሪቱ ዓመታዊ እቅዶችም ተዛብተዋል። ባለፈው ዐመት ለማካሄድ የተወሰነው ስድስተኛው አገር አቅፍ ምርጫ የተራዘመው በቫይረሱ ምክንያት ነው።
Be the first to comment