ሁለቴ የሞተው የትግራይ ሕዝብ!  | ዶ/ር ሔሮን ገዛኽኝ  

አንድ ማኀበረሰብ ከደረሰበት የአኗኗር ፍልስፍና አንጻር በየእለቱ የሚተገበሩ የተለያዩ ማኀበራዊ ሚናዎችን ትክክለኝነት የሚበይንበት መስፈርት እንደሚያበጅ የዘርፉ ባለሙያዎች ያስረዳሉ። እነዚህ የሚናዎች አግባብነት መመዘኛ መስፈርቶች ከማኀበረሰብ ማኀበረሰብ የተለያዩ መሆናቸውም ርግጥ ነው። የግለሰቦችም ሆነ የቡድኖች ማኀበራዊ ቅቡልነትምን መስፈርቶቹን ከማሟላት ጋር የተያያዘ ነው። መሰል መስፈርቶች በአንድ ዐይነት እና በብዝሃ ማኀበረሰብ ውስጥ መገኘታቸውም ተለምዷዊ ነው። አንዳንዶቹ ዓለም ዐቀፋዊነትን ተላብሰዋል። በብዝሃ ማኀበረሰብ የሚስተዋሉ መመዘኛዎች ድቅል አልያም ከአንድ ማኀበረሰብ የተቀዱ ናቸው። ይህም ሆኖ፣ በማኀበረሰቡ ዘንድ የታመነባቸውን መመዘኛዎች ማክበር የግድ ይላል።

ግና፣ እነዚህን ማኀበራዊ የጥሩነት ማረጋገጫ ብያኔዎች ማሟላት እና ተቀባይነትን ማረጋገጥ ለብዙዎች ቀላል አይደለም። ይህም ከፍ ላለ የሥነ-ልቦና ጫና መዳረጉ አይቀሬ ነው። በዚህ በኩል የሚከሰተው ድክመትም ለብዙ አውዳሚ ማኀበራዊ ግጭቶች ምክንያት የሆነበት አጋጣሚ በስፋት ይጠቀሳል። እንደ ባለሙያዎቹ ፍቺ፣ ይህን መሰሉ የሥነ-ልቦና ቀውስ “የበታችነት ችግር (In­feriority complex)” በመባል ይታወቃል።

ከበታችነት ጋር ተያይዞ የሥነ-ልቦና ችግር ሰለባ የሆኑ ሰዎች ወይም ቡድኖች ራሳቸውን አይረቤ አድርገው ሲቆጥሩ ይስተውላል። በዚህም፣ ማኀበራዊ ቅቡልነት ያላቸውን እነዚህን መስፈርቶች አሟልቶ ከመገኘት አልያም “ተዛቡ” የሚሏቸውን ጉዳዮች ነቅሶ ከማረም ይልቅ፤ “መስፈርቶቹን ያሟላሉ” በሚሏቸው ላይ ስር የሰደደ ጥላቻን ያዳብራሉ። ለተጠቁበት ችግር ዋንኛ መፍትሄ የሚያደርጉትም ማጠልሸት ወይም ማዋረድ ነው።

Continue reading

 

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*